ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ጎበኙ
********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ዛሬ ጎብኝተዋል።
ግድቡ በአንድ ጊዜ 2200 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል ሲሆን በዓመት ደግሞ 6 ሺህ ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።
የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም በአሁኑ ወቅት 36 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከኃይል ማመንጫነት ባሻገር ለቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆንም ይጠበቃል።
በግንባታ ላይ የሚገኘው የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአንድ ወር በፊት መጎብኘታቸው የሚያወስ ነው።
#EBC